እኔ ነኝ
ፀሃፊ ባልሆንም መፃፍ መብቴ ነው። አንባቢ ብትሆኑም አለማንበብ መብታችሁ ነው።
Sunday, April 26, 2015
ኡኡ...እላለው
አየሩ ቀዝቅዞ
ሰማዩ አርግዞ
ዝናቡ ክፍ ክፍ
ካፊያው ፊቴን ሲያርስ
በንፋስ ሽውታ
ሸሚዜ ሲፈታ
ከጋራው ጫፍ ሆኜ
እጆቼን ዘርግቼ
አይኖቼን ጨፍኜ
ኡ...ኡ...ኡ...ኡ
ኡ...ኡ...ኡ...ኡ
እያልኩ እጮሃለው
‘ነፃነትን ሃይል
የተፈጥሮን ዉበት
ስሜቴን መግለጫ
ቃላቶችን ባጣ።
Newer Posts
Older Posts
Home
Subscribe to:
Posts (Atom)