Sunday, April 26, 2015

ኡኡ...እላለው

አየሩ ቀዝቅዞ
ሰማዩ አርግዞ
ዝናቡ ክፍ ክፍ
ካፊያው ፊቴን ሲያርስ
በንፋስ ሽውታ
ሸሚዜ ሲፈታ
ከጋራው ጫፍ ሆኜ
እጆቼን ዘርግቼ
አይኖቼን ጨፍኜ
ኡ...ኡ...ኡ...ኡ
ኡ...ኡ...ኡ...ኡ
እያልኩ እጮሃለው
‘ነፃነትን ሃይል
የተፈጥሮን ዉበት
ስሜቴን መግለጫ
 ቃላቶችን ባጣ።

No comments:

Post a Comment